የራስ ተፈሪያን ማኅበረሰብ አባላት በሻሸመኔ

shashemene
May 2022

by Dawit Atreso

"…በሻሸመኔ ከተማ የሚኖሩት የራስ ተፈሪያን ማኅበረሰብ አባላት ሻሸመኔን ለቅቀው እንዲወጡ እየተደረጉ መሆናቸው እየተሰማ ነው። ኢትዮጵያን የነፃነት ቀንዲላቸው አድርገው የሚቆጥሩት ስረ መሠረታቸው ከጃማይካ የሚመዘዙትና ኢትዮጵያዊ ዜግነት አግኝተው የሚኖሩት ራስተፈሪያውያኑ በኦሮሙማው መንግሥት ድራሻችሁ ይጥፋ እንደተባሉ እየተገለፀ ነው። "…የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በኦሮሚያ ውስጥ በአሁኑ ጊዜ በነፃነት የሚለብሱት ጃማይካውያኑ ይሄን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ይዘው ሙጥኝ ማለታቸው በኦህዴድኦነጉ መንግሥት የተወደደ አይመስልም። አሁን በግሬደር ንብረታቸውን ፍርስርሱን እያወጡት እንደሚገኙ የሚደርሱኝ የቪድዮ መረጃዎች ያመለክታሉ።

"…ከ700 ዓመት ባርነት በኢትዮጵያ ድል ነፃ ወጣን ብለው ኢትዮጵያን ልብሳቸው አድርገው የሚኖሩት ራስታዎቹ ከ700 ዓመት በኋላ በዚያችው በኮሩባት ሃገራቸው በኦህዴድኦነግ ብልፅግና መንግሥት መዋረዳቸው እንዳሳዘናቸው የአይን ምስክሮች ይናገራሉ። "…ይሄ ጭራቅ ሰው ጠል ፖሊሲ በጊዜ ሃይ ካልተባለ በኦሮሚያ ምድር የሚተርፍ ዘር ያለም አይመስልም። ጃማይካውያኑ ግን እንደ ዐማራና ትግሬ ዝም ብለው ኢትዮጵያን ለፀረ ኢትዮጵያ ኃይል ትተው፣ እንደ ጉራጌ፣ ሲዳማና ወላይታ፣ ከንባታ ተረግጠው፣ እንደ አፋር ደቅቀው፣ እንደ ሱማሌ ታፍነው የሚቀመጡ አይመስሉም። ዓለም አቀፍ እንቅስቃሴ ሊጀመሩ መጠራራት ጀምረዋል። ኢትዮጵያውያንም አግዙአቸው። የሚያሳዝነኝ በእነዚህ ጥቂት ፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎች ምክንያት "ኦሮሞ አፈናቃይ ነው፣ አፍራሽ ነው፣ አሳዳጅ ነው፣ ወዘተረፈ ተብሎ በዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ የኦሮሞ ህዝብ መጠቆሩ ነው።